የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዘይት ባለ 5 ሊትር እና ባለ 1 ሊትር ብዛት 954 ፣ 1ኛ ደረጃ ፉርኖ ዱቄት ባለ 15 ኪሎ ግራም ብዛት 954፣ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ምስር ክክ፤ የተከካ የሽሮ እህል /አተር/ ጤፍ እና የተለያዩ አትክልቶችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር -ADV/197/25
የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዘይት ባለ 5 ሊትር እና ባለ 1 ሊትር ብዛት 954 ፣ 1ኛ ደረጃ ፉርኖ ዱቄት ባለ 15 ኪሎ ግራም ብዛት 954፣ መኮረኒ፣ ሩዝ፣ ምስር ክክ፤ የተከካ የሽሮ እህል /አተር/ ጤፍ እና የተለያዩ አትክልቶችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በመገኘት አዲስ አበባ ወሎ ሠፈር በኢትዮ-ቻይና መንገድ ወንገላዊት ህንፃ ፊት ለፊት ባለው መንገድ ማሪስቶፕስ ክሊኒከ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው:-
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)
- የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዘአብሔር ቤተክርስትያን የእርዳታና ልማት ማህበር ስም በአዋሽ ባንክ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሲ.ፒ.አ አሠርተው ከዋጋ ማቅረበያው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ፋይናንሻል ዶክመንት በፖስታ አሽገው መቅረብ አለባቸው:፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር ግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑት ዕቃውን በአንድ ሳምንት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሽሮ እህል እና ለምስር ክክ ሩብ ኪሎ ለፉርኖ ዲቄት 2 ኪ.ግ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዓርብ መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0949231127 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ማሳሰቢያ፡- አትክልት ያሸነፈው ድርጅት በ15 ቀኑ ለ3 ወራት ያለምንም ዋጋ ለውጥ ገፈርሳ ጉጂ/ ኬላ/ እና ቡራዩ በሚገኘው የምገባ ማዕከላችን አትክልቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዝአብሔር ቤተክርስቲያን የአርዳታና ልማት ማህበር
