Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቀ/ማረ/ቤት አስተዳደር/
  • Address ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-71-63-33
  • Website
  • Deadline03 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-03 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

በፈዴራል ማረሚያ የቀጠሮ ማረፈያ ማዕከል ቂሊንጦ ለህግ እስረኞች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን የጤፍ፤ የሽሮ እና የበርበሬ ወፍጮ አጠቃለው ሰርተው እንዲያስረከቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ


በፈዴራል ማረሚያ የቀጠሮ ማረፈያ ማዕከል ቂሊንጦ ለህግ እስረኞች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን የጤፍ፤ የሽሮ እና የበርበሬ ወፍጮ አጠቃለው ሰርተው እንዲያስረከቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡

  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡

  3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፣

  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ፡፡

  7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን/ፋይናንሻል ሰነዶችን/በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡

  8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም::

  9. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒአ ከቴክኒክ ሰነዶች ከአርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::

  10. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2017 .ም ከቀኑ 500 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

  11. ጨረታው መጋቢት 25 ቀን 2017 .ም ከቀኑ 530 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

  12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡

  13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በተለያየ ምክንያት ዝግ ከሆነ እና ዓመት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

አድራሻ ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ - 011 4 71 63 33 /01 18 88 60 89/011 434 89 86 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

/ማረ/ማዕከል/ቅልንጦ

 

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር

 

Save Tender