በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት በ2017 በጀት በካፒታል በጀት በወረዳው ለሚያስገነባው G+2 የአስተዳደር ሕንፃ የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን ወይም የሕንፃ መሣሪያዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት በ2017 በጀት በካፒታል በጀት በወረዳው ለሚያስገነባው G+2 የአስተዳደር ሕንፃ የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን ወይም የሕንፃ መሣሪያዎች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
-
በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን /ያላቸው
-
ለመንግሥት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
-
ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
-
መ/ቤቱ ካስቀመጠው ውጪ በራሱ ጊዜ እስፔስፊኬሽን የጨመረና የቀነስ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን ከ2፡30-6፡30 በተዘጋጀው ሣጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግልጽ ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 % በጥሬ ገንዘብ ወይም በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በሲፒኦ/ ማስያዝ አለበት፡፡
-
ተጫራቶች ከሚወዳደሩበት ሰነድ ላይ ከአንዱ ዋጋው እና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው /ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ፡፡
-
ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.አ/ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
-
መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግሥት ሥራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀንና ሰዓት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች ከኦርጅናል ሰነዱ ላይ የንግድ ፍቃዱን ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ የማያስገባ ወይም ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ ሳያስገባ ውጭ ላይ የተወ ከውድድር ውጪ የሚሆን መሆኑ ይታወቅ፡፡
-
ውድድሩ በጠቅላላ ድምር /ሎት/ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
