Tender Detail

Tender Details

  • Company Global Bank Ethiopia S.C (ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 558 12 04
  • Websitehttps://www.globalbankethiopia.com/
  • Deadline15 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-15 00:00:00
  • Categories

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አራት ቅርንጫፎች የአረንጓዴ ስፍራ እና የቴራዞ ማንጠፍ ሥራ ሕጋዊና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::


 

 ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

GLOBAL BANK ETHIOPIA

የቅርንጫፎች አረንጓዴ አትክልት ስፍራ እና የቴራዞ 

ማንጠፍ ሥራ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 17/2024/25

 

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አራት ቅርንጫፎች የአረንጓዴ ስፍራ እና የቴራዞ ማንጠፍ ሥራ ሕጋዊና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

 

ተ.ቁ

የአረንጓዴ አትክልት ስፍራ እና ቴራዞ ማንጠፍ ሥራ የሚሰራላቸው ቅርንጫፎች 

የጨረታ ማስከበሪያ

1

አያት ፀበል

 

ብር 20,000.00

2

አያት 49

3

መገናኛ 24

4

ቡልቡላ መድሃኒዓለም





 

 

 

 

 

 

 

በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከተውን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባንኩ ዋና መ/ቤት ናሽናል ታወር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ (ስታዲየም ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ::

  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚወስዱበት ወቅት የድርጅታቸውን የመስመር ወይም የሞባይል ስልክ ቁጥር በትክክል እና ግልጽ በሆነ መልኩ መጻፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል:: በትክክልና ግልጽ ሆኖ ባልተጻፈ አድራሻ ምክንያት ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ለሚተላለፍ መረጃ አለመድረስ ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም::

  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ በሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ያዘጋጁትን ሰነድ ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል::

  5. ጨረታው ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ተዘግቶ በዚያው እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡15 ላይ ይከፈታል::

  6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟሉ ከቀሩ ከጨረታው ይሰረዛሉ::

  7. ለመጫረት ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 558 12 04 ወይም 011 531 80 97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

  8. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

  

Save Tender