በ/ደ/ብ/ብ/ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት ለ2017ዓ/ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የካፒታል በጀት ለተለያዩ ዲ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎችን ከነሙሉ አክሰሰሪያቸው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በ/ደ/ብ/ብ/ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት ለ2017ዓ/ም የሥልጠና ዘመን በተመደበለት የካፒታል በጀት ለተለያዩ ዲ/ቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎችን ከነሙሉ አክሰሰሪያቸው በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች፣
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማረጋገጫ የሚያቀርብ፣ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የቲን ቁጥር /tin Number/ ያለው/ያላት፤
- በመንግሥት ግዥ አቅርቦት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
- የዕቃውን ዋጋ በኮሌጁ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ገፁን ሳይገነጣጥል ሞልቶ የሚያቀርብ
- የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ የዕቃዎችን መለያ /specification/ ኮሌጁ ባዘጋጀው መሠረት ብቻ የሚያቀርብ
- የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 / አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ጋር በማሸግ ማቅረብና ማስያዝ ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን / Bid Document/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአ/ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት ግ/ን/አስ⁄ ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ የስልክ ቁጥራቸውን ፣ ማህተምና አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- አጠቃላይ የማስረጃቸውን ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል የሚል ማህተም አርፎበት ተፈርሞበት ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
- የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሰነድ በሁለት ኮፒ ተዘጋጅቶ የዕቃው ነጠላ ዋጋ በአንድ በታሸገ እናት ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ቀን የሚያበቃው የሥራ ቀን ከሆነ በ15ኛ ቀን በ10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የታሸገው ሣጥን በአ/ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል ቀኑ በዓል (ዝግ) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፣ እንዲሁም ከስፔስፊኬሽን ውጭ ዕቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- አሸናፊዎች የዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ድረስ ማቅረብና ማስረከብ አለበት።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- የተጭበረበረ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም በሕግም ያስቀጣል፡፡
ለተጨማሪመረጃ-0468810960 /0910744129 / 0970727274 በደ/ብ/ብ/ኢ/ክ/መ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮአ/ምንጭፖ/ቴ/ሳ/ኢንስቲትዩት ደውለው ይጠይቁ
በ/ደ/ብ/ብ/ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትዩት
