በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዘመናዊ የህንጻ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ ለሚገኝ ደንቢ ትምህርት ቤት የፊኒሺንግ ሥራዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዘ.ህ.ኢ005/2017
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዘመናዊ የህንጻ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ ለሚገኝ ደንቢ ትምህርት ቤት የፊኒሺንግ ሥራዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
- ለመጫረት የሚመጡ ሕጋዊ ተወዳዳሪዎች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት፣ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የሚጠይቀውን የጨረታ ማስከበሪያ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ውስጥ በማካተት ማቅረብ አለባቸው።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ክፍለ ከተማ በዘመናዊ የሕንፃ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር ማርኬቲንግና ሽያጭ ክፍል ነው፡፡
ስልክ ቁጥር +251912148228/+251920711749 ወይም +251911957419
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ለአንባቢያን ከተሰራጨበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ትምህርት ቤቱ ያለበትን የግንባታ ሁኔታ የማየት መብታቸው የተፈቀደ ነው፡፡
- ጨረታው 16/8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ጨረታው በ16/8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ፡፡
- ተጫራቾች ለ90 (ለዘጠና) ቀናት የሚጸና የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ዋጋ 2 (ሁለት) ፐርሰንት በሲፒአ ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ የዋስትና ደብዳቤ ከአደራጃቸው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በኋላ ባሉ 5 (አምስት)የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ ውል መግባት አለበት።
- የአከፋፈል ሁኔታና ሥራዎችን አጠናቆ የማስረከቢያ ጊዜ በተዋዋዮች የጋራ የውል ስምምነት መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት ነው::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የዘመናዊ የህንጻ ኢንዱስትሪዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር
