በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል
- ባለጎማ ኤክስካቫተር ግሬደር፣ ዳምትራክ ፣ ሮለር እና ሎደር ማሸን ኪራይ (ተጫራቹ የኦፕሬተር አበል፣ የነዳጅ ፣ የቅባት ዘይትና ሌሎች ወጪዎችን ችሎ)
- የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ
- የተሽከርካሪና ማሽነሪ ጎማ፣
- የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት፣
- የህንጻ መሳሪያ፣
- ቢትመን፤
- የተፈጨ ጠጠር የግንብ ድንጋይ፣ ኮብልስቶን ድንጋይ እና አሸዋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የተሰጠ ወይም የታደሠ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘ ተጫራች የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በ16ኛው ቀን የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ /የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን /አርባ ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ግዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ያቀረበው የጨረታ ሰነድ ፖስታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ የሌለው ከሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሞላው ዋጋ የማይነበብና ተጫራቹም ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ መሙላት የሚችሉት መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙሊያ ሰነድ ብቻ ሲሆን በሌላ ወይም በራሱ የዋጋ መሙሊያ ሞልቶ ቢያቀርብ ተጫራቹን ከውድድር ውጪ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- በጨረታ በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለውና በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝና የማይነበብ ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ/ማሸነሪ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዥ ማስጫኛ እና ማውረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033 312 91 72/ 033 311 10 41/10 48/ 10 59 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ካራጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን
