በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ለምርት ማሸጊያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ካርቶኖች (Carton Box) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር APP /06/17
- በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ለምርት ማሸጊያ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ካርቶኖች (Carton Box) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- Carton Box 12.5-liter capacity (0.5 liter)
- Carton Box 10-liter capacity (0.25 liter)
- Carton Panel 317 mm*254mm
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉሙሩክ ሚኒስቴር በጨረታ እንዲሳተፉ የተጻፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኤምባሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኤምባሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመክፈል ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትክክል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል። ተጫራቾች ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በአዳሚ ቱሉ የፀረ- ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ መክፈቻው እለት ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል።
- ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ አ.አ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 662 4656 አ/አ፣ አዳሚ ቱሉ 046 441 9164 (ማዞሪያ)፤ 046 841 0447(ንግድ መምሪያ) ፖ.ሣ.ቁ 1206 (አ.አ)፣ 247 (አ/ቱሉ)
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ
