Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 025-4-11-65-51
  • Website
  • Deadline12 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-05-12 00:00:00
  • Categories

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ዲጂታል የሰራተኞች ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን (Biometric Attendance system and device) ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፦004/2017

 

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ //ቤት 2017 በጀት ዓመት ዲጂታል የሰራተኞች ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን (Biometric Attendance system and device) ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊና ብቃት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡ እያንዳንዱ የጨረታ ተካፋይ የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያ ነጥቦች በግልፅ በመረዳት በጨረታ ሰነዶች ላይ እንዲሟላ ማድረግ አለበት፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ለአንዱ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 04 ቀን 2017 . 300 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን በተጫራቾች የሚሞሉ ቅጾች ላይ ቅጾቹን በመሙላት ሙሉ ስማቸውን፤ አድራሻቸውን እና የሚጫረቱበትን ምድብ (ሎት) እንዲሁም ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው ሳጥን ግንቦት 04 ቀን 2017 . በተጠቀሰው ቦታ 330 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነዳቸውን በተናጠል ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከቴክኒካል የጨረታ ሰነዳቸው ጋር አካተው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
    1. ተጫራቾች በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ እንዲሁም VAT (የተጨማሪ እሴት ታክስ) እና TIN (የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ እንዲሁም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ግብር እና ታክስ ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው የሚሞላው በነጠላ ዋጋ ሲሆን፣ ዋጋው በእርሳስ ተሞልቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  6. ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ installation software cost, training cost እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ታሳቢ በማድረግ ዋጋ መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበት በነጠላ ዋጋ ላይ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ በግልፅ ያላስቀመጠ ተጫራች ዋጋው ቫትን እንዳካተተ ይቆጠራል።
  8. በተጫራቾች ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ግልጽና አጠራጣሪ ባልሆነ መልኩ መቀመጥ ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ የባለስልጣኑ (የድርጅቱ ባለቤት/ ተወካይ) ፊርማ የሌለበት ከሆነ ለአቅርቦቱ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሚንስቴር /ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የብር መጠን መሰረት ገቢዎች ሚኒስቴር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ /ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ CPO አልያም ደግሞ በጥሬ ገንዘብ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱ ዝርዝር ውስጥ በተጫራቹ ምርጫ ማስገባት ይኖርበታል።

 

.

የእቃው ዓይነት

የገንዘብ መጠን

1

ዲጂታል የሰራተኞች ሰዓት መቆጣጠሪያ ማሽን

20,000.00

 

  1. /ቤቱ የተጫራቾችን ብቃት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መስፈርቶች፣ የጨረታ መመሪያዎችና ሌሎችም ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ያካተተ ስለሆነ በሁሉም ተሳታፊ ተጫራቾች እንዲተገበሩ ያሳስባል፡፡
  2. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 025-4-11-65-51 ወይም 025-4-11-26-70 ደውለው መጠየቅ አልያም ሚያዝያ 18 ቀን 2017 . የወጣውን ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ //ቤት

 

Save Tender