በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒዬን የተለያዩ መጠን Calcium carbonate Filler (caco3) የተለያየ ቀለም ያለው Master Bach በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒዬን የተለያዩ መጠን Calcium carbonate Filler (caco3) የተለያየ ቀለም ያለው Master Bach በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም መሸጥ የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት ተወዳድሮ መሸጥ ይችላል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የአመቱን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢነት በሚመለከተው የመንግስት አካል ክፍል የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
- ለጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በዩኒዬኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000087184327 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000036818348 በመክፈል ሰነዱን ከዩኒዬን መውሰድ አለባቸው፡፡
- ለጨረታ ማስረከቢያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ ያቀረቡትን ዋጋ 5% በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ሰነድ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 12/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒዬኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን 12/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ዩኒዬኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ በሙሉ እስከ 10 ቀን ጊዜ ውስጥ ማስረከብ ይኖርበታል።
አድራሻ፦ በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
በስልክ ቁጥር 0113420265/0912129287 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የበቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒዩን ኃ/የተ/ማህበር
