የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን የተበጠረ ለምግብነት የሚያገለግል እህል በቆሎ ከሕጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን የተበጠረ ለምግብነት የሚያገለግል እህል በቆሎ ከሕጋዊ ነጋዴ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1ኛ ተጫራቶች በዘርፉ የታደሰ የ2017 ዓ.ም ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2ኛ ተጫራቶች የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ TIN ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3ኛ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ /ክሊራንስ/ የሚያቀርቡና አስፈላጊ የሆኑ ሕጋዊ ሠርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
4ኛ ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸውና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
5ኛ ተጫራቾች በንግድ ዘርፍ ያላቸውን ሰነዶች ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ ፖስታ በሰም በማሸግ እንዲሁም ቢሮው ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በሚነበብ ጽሑፍ በመሙላት የድርጅቱን ስም፣ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
6ኛ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ዶክመንት ፖስታ በታርጫ ከተማ በሚገኘው በደ/ም/እ/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በመገኘት በግዥ ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7ኛ የጨረታው ሳጥን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
8ኛ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም፡፡
9ኛ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
10ኛ ተጫራቾች አሸናፊ ድርጅት የእህሉን ዋጋ ሲሞሉ ትራንስፖርት እና ጫኝ አውራጅ ጨምሮ የሚሞሉና እስከ ታርጫ ከተማ መጋዘን ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
11ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በመ/ቤቱ ስም CPO /ጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
12ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት 1000521691305 ላይ ገቢ ተደርጎ ባንክ አድቫይስ ስታመጡ ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት መግዛት ትችላላችሁ።
13ኛ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-04-69-39-79/ 09-13-85-89-25 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
