የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሀርድ ኮር፣ ሴሌክትድ ማቴሪያል እና 02 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀርድ ኮር ፣ ሴልክትድ ማቴሪያል እና 02 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/34/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሀርድ ኮር፣ ሴሌክትድ ማቴሪያል እና 02 ጠጠር ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ክሊራንስ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸውና ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና CCRDA መካከል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ግብዓት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ጋራንቲና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን ፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና CCRDA መካከል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 0114621457
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
