የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የግንባታ ግብዓት፣ ማሸነሪዎችና የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች
ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 36/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የግንባታ ግብዓት፣ ማሸነሪዎችና የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች (ለ 1 ዓመት ውል በመፈፀም በሚቀርብ ፍላጎት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ)
- ሎት 2 የሳኒተሪ ዕቃዎች (ለ 1 ዓመት ውል በመፈፀም በሚቀርብ ፍላጎት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ)
- ሎት 3 የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣
- ሎት 4 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና
- ሎት 5. ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች (ለ 1 ዓመት ውል በመፈፀም በሚቀርብ ፍላጎት መሰረት ማቅረብ የሚችሉ)
ስለሆነም፡-
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራከሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የሎት አይነት ጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው የፍላጎት መግለጫ (specification) መሰረት ድርጅታችን ባቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ወይም በሶስተኛ ወገን ሊታይ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ፣ ለሎት 2 (የሳኒተሪ ዕቃዎች) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ፣ ለሎት3 (የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎች) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ፤ ለሎት 4 (ተሽከርካሪዎች) ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና ሎት 5 ሌሎች የግንባታ ግብዓቶች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት 1 ፤ ሎት 2 ፤ ሎት 3 እና ሎት 4 ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ እና ሎት 5 ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011-4-62-14-57
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
