የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም እና መከራየት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ ግዥ መፈጸም እና መከራየት ይፈልጋል፡-
ስለዚህ:-
-
- ሎት 1- የመኪና ና የማሸነሪ መለዋወጫ (ስፔርፓርት) እቃዎች
- ሎት 2 - የማሽነሪ እና የመኪናዎች ጎማና ባትሪ
- ሎት 3 - የማሽነሪ እና የመኪናዎች ቅባት እና ዘይት ግዥ
ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- ቲን ነበር ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናቶች በመንግስት የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ጨረታ በየሎቱ በእያንዳንዱ ማለትም ለሎት፣1- የማሽነሪና መኪና መለዋወጫዎች ስፔርፓርት ግዥ 30,000 ብር፣ ለሎት 2 - ጎማና ባትሪ ግዥ 20,000 ብር፣ ለሎት 3- የማሽነሪ እና የመኪናዎች ቅባት እና ዘይት 10,000 ብር ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ፤ በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በመሂ 1 የተቆረጠ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ሆኖ መረጃውን ፖስታው ውስጥ አስገብተው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጊዜ 40 የስራ ቀናቶች ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸው ቦታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመ ጊዜ ጀምሮ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙ ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ አይነት ዝርዝር ከሚገዙት ሰነድ ላይ ባለው የእቃ ዝርዝር መረዳት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ሰዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የለለበት ሲሆን የእቃው ናሙና ቢሮ ቁጥር 13 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድርግ የለባችሁም በተጨማሪም የዕቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥራችን 058 117 0033 ወይም 0581171208 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ:- ሁሉም ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀና በተጠየቀው ሞዴል መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያዎች መረጃዎች ካሉ በቢሮአችን በውስጥ ሰሌዳ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
