የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለህብረተሰቡ በሚደርሱ የአህል አቅርቦቶች ላይ እሴት በመጨመር ለሸማች ማህበረሰብ ለማሰራጨት የእህል መፍጨት አገልግሎቱን የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለእንድ ዓመት ውል በማስፈረም አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር- ኢንሥኮ‐ ማዕከል ግዥ
ብ/ግ/ጨ/016/2017
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለህብረተሰቡ በሚደርሱ የአህል አቅርቦቶች ላይ እሴት በመጨመር ለሸማች ማህበረሰብ ለማሰራጨት የእህል መፍጨት አገልግሎቱን የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለእንድ ዓመት ውል በማስፈረም አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተለያዩ የምርት ዓይነቶች (ስንዴ፣ በቆሎ፣ እና ጤፍ) እህል የመፍጨት አገልግሎት ግዥ፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች የቴክኒክ ሰነዶችን የ2017 የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዘገባ ሰርተፊኬት፣ ወቅታዊ የግብር ክሊራንስ ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢዎች ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እነዚህ ሰነዶች ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀን ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት ጨረታ የማይመለስ ብር 400.00 (ብር አራት መቶ) በመክፈል ከሰኔ 4 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት ከ7:30-11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡30 ድረስ ብሎክ 1 ቁጥር 206 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ (አድራሻው ከስር ተገልጿል፡፡)
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የአገልግሎት ዋጋ (ፋይናንሻል) ቴክኒካል ፤ ኦሪጅናል በመለየት በአንድ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የተለያዩ የምርት ዓይነቶች (ስንዴ፣ በቆሎ፣ እና ጤፍ) በ5 ኪግ፣ 10 ኪ.ግ፣ 15 ኪ.ግ 25 ኪ.ግ እና በ50 ኪግ እህል የመፍጨት አገልግሎት ግዥ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም ሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ስልክ 011 4167345/011 466 9336
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
