Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለዲስትሪክቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1. ጀነሬተር 100KVA ብዛት 1፤ ሎት-2. የኮንክሪት ሚክሰሮችን ብዛት 3፣ ሎት-3 የማሽነሪዎች እና የከባድ መሳሪያዎች መፍቻ (Heavy Duty Tool Set) ብዛት 2 እና የቀላል ተሽከርካሪዎች መፍቻ (Light Duty Tool Set) ብዛት 2 በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር -02/2017

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለዲስትሪክቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1. ጀነሬተር 100KVA ብዛት 1 ሎት-2. የኮንክሪት ሚክሰሮችን ብዛት 3 ሎት-3 የማሽነሪዎች እና የከባድ መሳሪያዎች መፍቻ (Heavy Duty Tool Set) ብዛት 2 እና የቀላል ተሽከርካሪዎች መፍቻ (Light Duty Tool Set) ብዛት 2 በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታክስ ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ሰነዶችን በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በኢትጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000496010117 ERA GODE DISTRICT ገቢ በማድረግ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና /ቤት በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታውን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና /ቤት ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።
  4. ተጫራቾች ለሎት1. ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ለሎት 2. እና ለሎት-3. ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በገንዘብ ያዥ በተፃፈ ቼክ (CPO) ከሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተቀባይነት የለውም።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና /ቤት በግልፅ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታ መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ግዥ፣ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቡድን

ስልክ ቁጥር ሞባይል 0914112484 / 0916012196 / 0911248669

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎዴ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

 

Save Tender