በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የተለያዩ ያገለገሉ ቆርቆሮና ኤጋ ቆርቆር ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2017ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን የተለያዩ ያገለገሉ ቆርቆሮና ኤጋ ቆርቆር ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከተውን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በግልጽ ጨረታው በቀረበው ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተለያዩ ያገለገሉ ቆርቆሮና ኤጋ ቆርቆር ባለበት ሁኔታ በማየት መጫረት ይቻላል።
- በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ፊት ለፊት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ክፍያና ሂሳብ ቡድን በመምጣት የንብረቱን ዝርዝር መመሪያ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሰነድ በመግዛት ሊመለስ በማይችል ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምር ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቱን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በአሃዝ አና በፊደል በሰጠው የዋጋ መሙያ በመሙላት ማስገባት ሲችሉ ልዩነት ካለው ከፍተኛ ዋጋ በመውሰድ ያወዳድራል።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር ተከታታይ የስራ ቀናቶችን ታሳቢ በማድረግ ያሉ ቀናቶችን ታሳቢ በማድረግ በ11ኛው ቀን የሰነድ ሽያጭ ተጠናቆ በ11ኛው ቀን ማለትም ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾችን ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን ቢሮ ላይ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታው መከፈት ኢያስተጓጉልም።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7/ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪ ክፍያውን በማጠናቀቅ ያሸነፈበትን ንብረት በ5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል። የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት አለበት።
- የንብረቶቹ የጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦች ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
- አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ለተመደበው ዕቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል እና ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች እና መነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ (10%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረታቸውን በ5/አምስት/ ቀናት ማንሳት ይኖርባቸዋል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 827 5923 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- መድሃኒአለም ከራስ ሃይሉ መዝናኛ ማዕከል አጠገብ አዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን 4ኛ ቢሮ ቁጥር 401 ፎቅ ፊት ለፊት በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 401 4ኛ ፎቅ ፊት ለፊት የንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቡድን
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
