የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ድራማዎች (ለቴሌቪዥንና ሬዴዮ) NCB 0016/2017 በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር NCB-0016/2017
የተለያዩ ድራማዎች (ለቴሌቪዥንና ሬዲዮ) NCB 0016/2017 ግዥ ጨረታ
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ድራማዎች (ለቴሌቪዥንና ሬዴዮ) NCB 0016/2017 በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት መረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገበበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የቲን ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 20,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼከ፣ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስምሞልተው ከኦሪጅናል ቴከኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋና የቴክኒክ መግለጫዎች አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ በታሸ ኤንቨሎፕ በማድረግና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 8፡30 ተዘግቶ ከቀኑ 8፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0115172521/11 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
