Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Media Network (AMN) (የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ)
  • Address 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም ቤ/ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ። ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 1116382
  • Websitehttps://www.amn.gov.et/ Website
  • Deadline07 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-07-07 00:00:00
  • Categories Art , Media

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በ2017 በጀት ዓመት የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 2017 በጀት ዓመት የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሠረት፡-

ሎት 1. የአማርኛ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ አገልግሎት ግዥ

ሎት 2. የአፋን ኦሮሞ ተከታታ የቴሌቪዥን ድራማ አገልግሎት ግዥ

በጨረታ ቁጥር .......010/2017 በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ በመሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ -

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የገቢዎች ክሊራንስ ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና በግዥ አቅራቢነት የተመዘግቡ፡፡
  3. ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ እና ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማቸውን ማኖር ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለእያንዳንዱ ለሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 በባንክ በተረጋገጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1-2ላሉት ጨረታዎች 10 የስራ ቀናት ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ቢሮ ቁጥር 28 2ፎቅ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም። የመክፈቻው ዕለት በዓል/ዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋናውንና ኮፒውን/ ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  8. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
  9. በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ከመ/ቤታችን ጋር ጨረታውን እንዳሸነፈ ካወቀበት ጊዜ አንስቶ 15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርበታል።
  10. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ 5 ኪሎ ቅድስት ማሪያም /ክርስቲያን ከማህበረ ቅዱሳን ጀርባ ያለው ህንፃ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 0111 11 63 82 መደወል ይችላሉ።

 

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ

 

Save Tender