የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሀርድ ኮር፤ ፑሚስ (ኮሚቼ)፤ 00 ጠጠር፤ ቀይ አሸዋ (Red Ash) እና የግንብ ድንጋይ ከነትራንስፖርቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ውል ፈፀሞ የተጠቀሰውን የግንባታ ግብዓት ማቅረብ ከሚችሉ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/39/2017
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሀርድ ኮር፤ ፑሚስ (ኮሚቼ)፤ 00 ጠጠር፤ ቀይ አሸዋ (Red Ash) እና የግንብ ድንጋይ ከነትራንስፖርቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ውል ፈፀሞ የተጠቀሰውን የግንባታ ግብዓት ማቅረብ ከሚችሉ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ፣ ክሊራንስ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ ኢያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኢሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና CCRDA መካከል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ግብዓት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ጋራንቲና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በድርጅቱ የመሰብስቢያ አዳራሽ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን ።
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና CCRDA መካከል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 0114 62 14 57
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
