በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውሉ የምግብ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሬስቶራንት የምግብ ግብዓቶች ጨረታ ቁጥር 03/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውሉ የምግብ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው በማወዳደር ግብዓቶቹን መረከብ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸውን የሚገልጽ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፤ የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፣ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለፅ አለበት፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመጫረቻ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ፋ/ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ አድርገው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማዕከሉ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የዕቃዎችን ዋጋ በማስፈር ማቅረብ እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲፒኦ 5,000 / አምስት ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በ10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ከተባለው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማስታወቂያው ከወጣበት 10ኛው (ጨረታው በሚከፈትበት) ቀን 4፡30 እስከ 5፡30 ባለው ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተባለው ሰዓት ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች በሙሉ/በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸንፉበትን ዕቃ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገለፃል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዕከሉ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም ከመድኃኒያአለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትልቁ አደባባይ ወደ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተ ግራ ገባ ብሎ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
