የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለአርሲ ዞን ቡሳ ጎነፋ ቅርንጫፍ የተለያዩ ጥሬ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለአርሲ ዞን ቡሳ ጎነፋ ቅርንጫፍ የተለያዩ ጥሬ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን።
ስለዚህ፡-
- ማንኛዉም ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 20 ፐርሰንት የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በመስራት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በመግዛት ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0222381142 ደውለው ይጠይቁ።
የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
