Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethio Life and General Insurance S.C (ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ, ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቶሊፕ ሆቴል ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት, Phone: 0114702077
  • Websitehttps://eliginsurance.com/
  • Deadline02 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazine ሪፖርተር
  • Bid Document Price
  • opening date2025-09-02 00:00:00
  • Categories

የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. ለቢሮ፣ ለንግድ ወይም ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

በድጋሚ የወጣ የህንፃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 0004 /2017

 

  1. የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ .. ለቢሮ፣ ለንግድ ወይም ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
  2. ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ የሕንፃ ባለቤቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች እና ሰነዶች በማሟላት በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለ ክፍያ በመውሰድ በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛችኃል፤ ይጋብዛል
  3. የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ .. ሊገዛ የሚፈልገው ሕንፃ፡
    1. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከዋና መንገድ ዳር (ከመንገድ ያለው ቅርበት በኮሪዶር ልማት ፕሮጀክት መሰረት የሆነ) ወይም ከዋና መንገድ ብዙ ያልራቀ፤
    2. የሕንፃው ዓይነት፡ ለቢሮ፣ ለንግድ ወይም ለቅይጥ አገልግሎት መዋል የሚችል፤
    3. የቦታው አጠቃላይ ስፋት 500 ካሬ ሜትር የማያንስ፤ የአረንጓዴ ቦታ ስፋት 100 ካሬ ሜትር ያላነሰ፡ እና ጠቅላላ ህንጻው ያረፈበት ቦታ ስፋት 400 ካሬ ሜትር የማያንስ፤
    4. የመኪና ማቆሚያ፡ ቢያንስ 20 መኪኖችን ማቆም የሚችል
    5. ሕንፃው ያለበት የግንባታ ደረጃ፡- 70 በመቶው ወይንም ከዛ በላይ የተጠናቀቀ ሆኖ 12 ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ የሚችል፤ ወይንም ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ፤
    6. በተጨማሪም ሊፍት፣ የደረጃ መወጣጫ፣ የውሃ ታንከር፣ የእሳት አደጋ መከላለከያ፣ የአደጋ ጊዜ መውጫ፣ ሦስት ፌዝ የኤሌትሪክ መስመር እና የዳታ መስመር ያለው፤
  4.  ይህ የሕንፃ ግዢ ጨረታ ከነሐሴ 18 ቀን 2017 . ጀምሮ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2017 . ድረስ 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 430 ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮ ላይፍ እንድ ጀኔራል ኢንሹራን .. ዋና መስሪያ ቤት የስልጠና አዳራሽ (8 ፎቅ) ይከፈታል
  5.  ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሀሳብና የፋይናንስ ዋጋ ነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው መሰረት በሚከተለው አድራሻ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስታወቂያ ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6.  ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀኔራል ኢንሹራን .. ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ ..

የሰው ሃብትና ፋሲሊቲ ማጅመንት መምሪያ

መስቀል ፍላወር አካባቢ ከሴንራል ማተሚ ፊት ለፊት

ሆም ኦፍ ሚሊዮንስ ህንጻ

ስልክ፡ 0115549650/51 አዲስ አበባ

 

Save Tender