የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት፡-
በድጋሚ ጨረታ የወጡ የአቃ/የአገልግሎት ግዥ፡-
ሎት 1 - የፈረንጅ እንቁላላ አቅርቦት ግዥ፤
ሎት 2 - የወተት አቅርቦት ግዥ፤
ሎት 3 - የማር ጠጅ አቅርቦት ግዥ፤
ሎት 4 - የሥጋ ቤት ቦታ ኪራይ፤
ሎት 5 - የአይብ አቅርቦት ግዥ፤
ተጫራቾች የሚከተሱትን መመሪያዎች ማሟሳት/ ተግባራዊ ማድረግ አስባቸው::
-
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሃገር ውስጥ ገቢዎች የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ማንኛውም ተጫራች ለሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ/ ብር እና ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3 እና ለሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
-
ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፤ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡
-
ጨረታን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን እሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
-
ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
-
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያe በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid Document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባ- ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒ CPO ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
-
የጨረታ ሂደቱ የቴክኒካል ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካ ሰነድ ግምገማ ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ለሎት 1፣ 2 እና ለሎት 3 ቴክኒካል ግምገ ውጤት 60 እና የፋይናንሽያል (ዋጋ ግምገማ ውጤት 40% ሲሆን እንደዚሁም ለሎ- 4 እና ለሎት 5 ቴክኒካል ናሙና ጥራትና ስፔስፊኬሽን ግምገማ ውጤት 40% የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት 60% ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ጥራት ግምገማ ሠነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከራ እንዲታወቅ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በመሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-5-53-07-67/ 011-5-15-73-37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
