ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ለሕንጻ እድሳት አገልግሎት የሚውል አልሙኒየም አቅርቦ የሚሠራ ባለሙያ (ድርጅት) ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ለሕንጻ እድሳት አገልግሎት የሚውል አልሙኒየም አቅርቦ የሚሠራ ባለሙያ (ድርጅት) ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው።
- የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ቅዳሜ ከ3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ አክሲዮን ማህበሩ ገንዘብ ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱንና የተጫራቾች መመሪያ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ16ኛ (አስራ ስድስተኛ) የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) በእከሲዮን ማህበሩ አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ዋስትና) ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ /ሲፒኦ/ በታህሰብ የንግድ ስራዎች አከሲዮን ማህበር ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- አሸናፊው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የስራ ውል መዋዋል አለበት።
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ፡-
- ስልክ ቁጥር 0112-79-30-65/0112-80-41-96
- አድራሻ ክልል አዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኮልፌ አጠና ተራ ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር
ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አክሲዮን ማህበር
