በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውል የምግብ እቃዎች እና ጥሬ ግብዓቶችና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሬስቶራንት የምግብ ግብዓቶች ጨረታ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ለ2018 ዓ.ም ለሬስቶራንት አገልግሎት የሚውል የምግብ እቃዎች እና ጥሬ ግብዓቶችና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከታች የተገለጸውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው በማወዳደር ግብዓቶቹን መረከብ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸው የሚገልፅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ህጋዊ በሚወዳደርበት ዘርፍ የንግድ ፈቃድ (የአቅራቢ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ፤ የሻት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፣ የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸው መገለፅ አለበት።
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስም እና ፊርማ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርባቸው የጨረታ ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ፋ/ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አድርጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ማእከሉ ባወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ የምግብ ግብዓቶች ዋጋ በማስፈር የማቅረብ እና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲፒኦ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ከ10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልፅ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- ከተባለው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ማእከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው (ጨረታ በሚከፈትበት) ቀን 4፡30 እስከ 5፡30 ባለው ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተባለው ሰዓት ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ይሰረዛል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ያሸንፉበትን ግብዓት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ለሚመለከተው አካልም በደብዳቤ ይገልፃል።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት ማእከሉ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
አድራሻ፡-
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተግራ ገባ ብሎ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከል
