በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከካፒታል በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለኮሪደር ልማት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከካፒታል በጀት ለኮሪደር ልማት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን ማለትም ሲሚንቶ፣ ብረት እና ተያያዥ ዕቃዎች በሎት1 /አንድ/ እንዲሁም ድንጋይ፤ አሸዋና ጠጠር የመሳሰሉትን በሎት2 /ሁለት/ እንዲሁም ለቁጠባ መገንጠያ አስፓልት መንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን ማለትም ሲሚንቶ፤ ብረት፤ እና ተያያዥ ዕቃዎችን በሎት 3 /ሶስት/ እንዲሁም
ድንጋይ፣ አሸዋና ጠጠር የመሳሰሉትን በሎት 4 /አራት/ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- የክፍያ ማዘዢያ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት። በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው።
- 4 በጨረታ ለመሳተፍ የሚያግለግል ከገቢዎች የተጻፈ ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 15% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት /በጥቅል/ ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ8/02/2018 ዓ.ም እስከ 22/02/2018 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 23/2/2018 ዓ/ም ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ከ23/02/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ላይ ይከፈታል ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37/033 551 05 04/ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት የማጭብርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበት ቅጽን ፈርሞ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት፡፡
የመሥሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንጻ እምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነው
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት
