የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሕንፃው ጐን በሚገኘው ቦታ የአፈር ምርመራ በማድረግ ግንባታ ለማስጀመር ዝግጅት ላይ በመሆኑ ከፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ በኤጋ ቆርቆሮ እንዲታጠር ስለተፈለገ ከታች በተዘረዘረው ስፔስፊኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሕንፃው ጐን በሚገኘው ቦታ የአፈር ምርመራ በማድረግ ግንባታ ለማስጀመር ዝግጅት ላይ በመሆኑ ከፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ በኤጋ ቆርቆሮ እንዲታጠር ስለተፈለገ ከታች በተዘረዘረው ስፔስፊኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ፊት ለፊት የሚገኘው የአጥር ርዝመት 28ሜ
- የአንድ ኤጋ ቆርቆሮ ስፋት 0.90 ሳ.ሜ
- የአንድ ኤጋ ቆርቆሮ ርዝመት 4 ሜትር
- የሚያስፈልገው የኤጋ ቆርቆሮ ብዛት በቁጥር 35
- ባለ 30 ጌጅ ናቸው።
በዚሁ መሠረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የታደስ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፤ የቲን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ፋይናንሻል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰባተኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቆርቆሮ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- ፌዴሬሸኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
ለበለጠ መረጃ፡- 0911-46-22-60/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ፋክስ-0116-45-08-79
ፖ.ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
