በሀገር መከካከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምረያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የምልምል ሰልጣኝ ወታደሮችና በሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የተጣራ የበሬ ስጋ እና የበቆሎ ቅንጬን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከካከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምረያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የምልምል ሰልጣኝ ወታደሮችና በሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የተጣራ የበሬ ስጋ እና የበቆሎ ቅንጬን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው
1. ተጫራች በዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
5. የዘመኑ ግብር የከፈለ /ከሊትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
6. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች/ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራች የአንድ ዋጋ መሙላት ያለበት ያለ ቫት ሆኖ ሁሉንም ቀለቦች ዋጋ በሙላት ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
9. በጨረታ አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው ዝርዝር በተናጠል ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመረጣል፡፡
10. በሰነዱ ሳይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል፣፣
11. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
12. ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
13. የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
14. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በስራ ቀንና ሰዓት ከ02/03/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 11/3/08 ዓ/ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
15. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ12/3/08 ዓ/ም ከጥዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው፡፡ በዚሁ ቀን 12/03/2018 ዓ/ም ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
16. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በየሳምንቱ፣ በየ15 ቀኑ ወይም በየወሩ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ቀለቡን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ የቀለቡን ጥራት የጥራት ኮሚቴው ካለተቀበለው ከ3-5 ባሉት ቀናት ውስጥ ቀይሮ ጥራት ያለው ቀለብ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
17. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ የአቅርቦት ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሪጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
18. የውል ስምምነቱ ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ ከ5-6 ወራት ድረስ ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው ማዘዣ መሰረት እየቀረበ የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል። የዋጋ ማሻሻያም አይደረግበትም፡፡
19. ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
20. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
21. በዚህ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በስራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይችላሉ።
ብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማ/ት/ቤት
