ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/የአገልግሎት ግዥ
ሎት-1. ተቆልቶ የተፈጨ ቡና አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017/2018 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፤ የነቢዎች ክሊራንስና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለበት፡፡
- ለጨረታ ሰነድ መሃዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽ አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ስነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፈርማቸውን፣ ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ መገለጽ አለበት።
- ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ሲዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመቶ በመጨመር ወይም 20% በመቶ ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴክኒካል ሠነድ ግምግማ ድርጅታዊ ብቃት እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት 60% እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት 40% ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፤ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ሠነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት ማወቅ አለባችሁ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 5 53 07 67/011 5 15 73 37 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
