የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣በኮፈሌ እና በአሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ
ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - ኢምዘደውአዘ/ጨሽ/ 01 ሠነድ/2018
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣በኮፈሌ እና በአሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ ፡-
1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግስት ግብርየከፈሉ፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንከ በተረጋገጠ በCPO ብቻ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲሰ
አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፤
5. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት ፡፡ ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
8. የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሠነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል፡፡
9. ዋጋውን በኢንቬሎብፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ጽ/ቤት አዳራሽ እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011 6 18 61 25 አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
