በምዕራብ ሸዋ ዞን ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን በመጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ጊዜው ያለፈባቸው ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ እና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተለያዩ ፀረ አረም እና የዋግ መድሃኒት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ እና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተለያዩ ፀረ አረም እና የዋግ መድሃኒት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን በመጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ጊዜው ያለፈባቸው ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ እና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተለያዩ ፀረ አረም እና የዋግ መድሃኒት በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት፤ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው
- ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ (Expired) እና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ፀረ አረምና የዋግ ኪሚካል የስራ ፍቃድ ያለው እና የ2018 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፈቃድ፣ TIN, ግብር ስለመክፈሉ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንደማያቀርቡ እና አቅርበው የሚገኙ ከሆነ በህግ ስለመጠየቃቸው የሚያስረዳ ደብዳቤ ለሮቢ በርጋ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ፣የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 8%-CPO በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንከ እና ንግድ ባንክ በሮቢ በርጋ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ስም ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፤ የጨረታው ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ሲመለስ፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በዩንዬኑ መጋዘን በአካል በመገኘት የምርት ግብዓቶቹ ያሉበትን ሁኔታ በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 2,000 በመግዛት፣ ለእያንዳንዱ ለሚገዙት ግብዓት የሚገዙበትን የአንድ ኩንታል እና ሊትር ዋጋ በብር መስጠት አለባቸው፤
- ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት ፊት ወይም ባይገኙም ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4:05 ሰዓት ጠዋት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ እና ፀረ አረምና የዋግ መድሃኒት በዩንዬኑ መጋዘን ውስጥ ተሰብስቦ የሚገኘውን በመለየት በወቅቱ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የሚረከብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎችን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተም፣ ስም እና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ በጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ሆለታ ከተማ ግብርና ምርምር በሚወስደው መንገድ
ስልክ ቁጥር፡- 09-13-92-79-93
የሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ
