Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Investment Commission (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ሜክሲኮ ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-78-46
  • Websitehttps://investaddisababa.com/
  • Deadline12 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-12 00:00:00
  • Categories Project Work

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንቨስትመንት ልማት ጥናትና ፕሮሞሽን አገልግሎት የሚውሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ 002/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንቨስትመንት ልማት ጥናትና ፕሮሞሽን አገልግሎት የሚውሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን የምዝገባ የምስ ወረቀትና ሌሎች ለጨረታ መወዳደር የሚያስፈልጉ ተጨማሪ መረጃዎች፣

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከታች ለተዘረዘሩት የፕሮጀ ጥናቶች

1.     Ready-mix concrete plant

2.     Electric charge station

3.     Organic fertilizer manufacturing

4.     General purpose manufacturing assembly plant

5.     Electric battery charge production

6.     Solar energy plate production

7.     Fibber glass production

8.     Catering service delivery

9.     Mobile electric charge

10. Epoxy chemical production በሠነዱ በተገለፀው መስፈርት መሰረት

በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት /ቤት የዋስትና ደብዳቤ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች 10ሩንም ወይም በሚፈልጉት ብዛትና ዓይነት መጠን መወዳደር ይችላሉ፡፡

4.     አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀበት 5 /አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ 6 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት።

5.     መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነድ/ዶክሜንቱን ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብቻ በመፈል መግዛት ይችላሉ።

6.     ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ 11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 359 ሰዓት ድረስ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሠንጋ ተራ ዮቤከ ህንፃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7.     ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሠንጋ ተራ ዮቤክ ህንፃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ግዢ ዳይሬቶሬት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ በዕለቱ ይከፈታል።

8.     ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናልና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) በፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።

10. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም።

11. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል።

12. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

አድራሻ፡- ልደታ ከፍለ ከተማ ሜክሲኮ ሠንጋ ተራ ዮቤከ ህንፃ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

 

ለበለጠ መረጃ በስ..011-5-57-78-46 እና 0913-04-5738 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

 

Save Tender