በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ለምርት ግብዓት የሚውሉ ጥሬ ዕቃ እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ለምርት ግብዓት የሚውሉ ጥሬ ዕቃ እቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
|
No |
Description |
Kg |
|
1 |
Ldpe Middum Duty |
86,900 |
|
2 |
Pvc Resin |
132,580 |
|
3 |
PP Raffia |
37,000 |
በመሆኑም ተጫራቾች:-
- በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኢንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጠል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለፅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የሚዘጋጀው የጨረታ ማሰከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም
- ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው
- ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩኘ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
አዲስ አበባ
