Tender Detail

Tender Details

  • Company የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
  • Address ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት የሚገኘው የአስተዳደር ህንፃ 9ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0944-31-17-95
  • Website
  • Deadline15 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2025-12-15 00:00:00
  • Categories

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ማለትም፡- (ሎትı) የተለያየ ዝርያ ያላቸው ዶሮዎች (ሎት2) የዳልጋ ከብቶች (በሬዎች) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋ/ስ/አስፈጻሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዥዎች ማለትም፡-

(ሎትı) የተለያየ ዝርያ ያላቸው ዶሮዎች

(ሎት2) የዳልጋ ከብቶች (በሬዎች) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ

5. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በየሎቱ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት ለአሸነፈባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፤ CPO ሲያሰሩ ለአቃ/ቃ/ከ/ከ/ዋና/ስ/አስፈጻሚ ፋይናንስ ቡድን ወይም AK/K/S/C/C/Executive finance team/ ብለው ያሠሩ (ሎት.1)50,000.00 (ሃምሳሺህ ብር) (ሎት.2)30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) አሰርታችሁ

ማቅረብ ያለባችሁ መሆኑን እያሳወቅን ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚገዙትን ግዥዎች ዝርዝርየያዘውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 9ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ክቫት በፊት ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት በታሸገ ኤንቨሎፕ እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ ለማስገባት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ከገዙት ሰነድ ወጪ በሌላ ሠነድ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

7. ጨረታው ከአስረኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. ለተጨማሪም መረጃ በስልከ ቁጥር 09 44 31 17 95 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ኣማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት የሚገኘው የአስተዳደሩ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ላይ ነው::

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት

 የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን

Save Tender