የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የማሽነሪ ዕቃዎችን በኪራይ ወስደው የነበሩ እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱ ተከራዮች በሊዝ ውሉ መሰረት የሊዝ ክራይ ክፍያውን ባለመክፈላቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዮቹ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የማሽነሪ ዕቃዎችን በኪራይ ወስደው የነበሩ እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሱ ተከራዮች በሊዝ ውሉ መሰረት የሊዝ ክራይ ክፍያውን ባለመክፈላቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/90 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራዮቹ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
የካፒታስ ዕቃ ተከራይ ስም |
የሚሸጠው ንብረት |
ብዛት |
የድርድሩ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የሚሽጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
ድርድሩ የሚካሄደበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
|
ኢሳኮር አግሮ ኬሚካል ኃላ/የተ/የግ/ማህበር |
የግብርና ኬሚካል ማምረቻ ማሽን |
1 |
54,790.927.23 |
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሞጆ ከተማ በድርጅቱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ |
በባንኩ አዳማ ዲስትሪከት መ/ቤት ውስጥ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም 4:00-6:00 |
|
ሳሙኤል ተስፋዬ (ኢትዮ ሪሳይከለንግ) |
የእንቁላል መያዣ እና ለተለያዩ ምርቶች /corpugated paper box የሚያመርት ማሽን እና ጄኔሬተር |
1 |
4,491.726.84 |
ቢሾፍቱ ከተማ ባንኩ በቋሚነት የተረከበው የአቶ ሽመልስ ካሱ ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ውስጥ |
በባንኩ አዳማ ዲስትሪክት መ/ቤት ውስጥ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-6:00 |
1. ተደራዳሪዎች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መደራደር ይችላሉ፡፡
2. ተደራዳሪዎች የድርድር ጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጰያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪከት በመውሰድ የሚገዙትን የካፒታል ዕቃ እና የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተራ ቁጥር 1 እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ እና ለተራ ቁጥር 2 እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው::
3. በጥሬ ገንዘብ አሸናፊ የሆነው ተደራዳሪ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታከስ /NAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የድርድር ጨረታ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡
4. ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጀቶችን በመወከል በድርድር ጨረታ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጣ ዋና የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. ካፒታል ዕቃውን መልሶ መከራየት የሚፈልግ ተበዳሪ የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ማሟላት እና ንብረቱን የሚከራይበትን ዋጋ እና ስለ ቀሪው ኪራይ አከፋፈል ሁኔታ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማሰገባት ይኖርበታል፡፡
6. አሸናፈው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተደራዳሪዎች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
7. የድርድሩ አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መበት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል ይገደዳል::
8. የድርድር ጨረታው አሸናፊ 15% የተጨመሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን አንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
9. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰውን ማሽን አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን ካለበት መጋዘን ነቅሎ መውሰድ አሊያም ከይዞታ ባለቤቱ ጋር መስማማት ይኖርበታል፡፡
10. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንከ አዳማ ዲስትሪከት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 022-212-04-17 ላይ መደወል ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪከቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
11.ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሃራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
