የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር እና የድልድይ ቤሪንግ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2017
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር እና የድልድይ ቤሪንግ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው አንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፤
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN/ ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- የሚገባው ማጠናከሪያ ብረት፣ ሚስማር፣ እና የድልድይ ቤሪንግ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 በመክፈል የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ከቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታውቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ30/03/2018 ዓም ጀምሮ እስከ ቀን 15/04/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ አርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ እድርገው ማስያዝ አለባቸው ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ ማስገባት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ አፊሰር : ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 30/03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 15/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታከስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጭን ጨምሮ መሆን አለበት፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ አፊሰሮች ቢሮ በ15/04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ አፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፣
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፣
- ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582221100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583205155/0582221107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
ባህር ዳር
ፖ.ሣ.ቁ.382
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
