የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፤ ግንባታና ማማከር ድርጅት Ready mix concrete C-25 and C-30 with Pump and accelerator chemical ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት Ready
mix concrete with Pump and accelerator chemical ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 04/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፤ ግንባታና ማማከር ድርጅት Ready mix concrete C-25 and C-30 with Pump and accelerator chemical ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፣
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራከሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ግብአት በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት የፍተሻ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (un conditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቢያንስ ለ 6 ወር ውል ተዋውለው የመስራት አቅም ያላቸው እና እንደ ሁኔታው ውሉን ለማራዘም ፍቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ ስልክ ቁጥር 09-13-56-49-36/ 0911-15-60-36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
