ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ የማሽን መለዋወጫ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀገር ውስጥ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ የማሽን መለዋወጫ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፍኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺል ሰነዶችን በአንድ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ/የግዥ ክፍል ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዝግ ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል።
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011 15 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ፡- 0115 51 86 96 ፖ.ሳ.ቁጥር 2365
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
