Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 111 61 34
  • Website
  • Deadline28 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-12-28 00:00:00
  • Categories Equipment

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊመንግስትየደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ያለአገልግሎት የተቀመጡ የቢሮ እቃዎች፣ ብረታብረቶች ፤ ያገለገሉ የጤና ጣቢያ አልጋዎች እንዲሁም ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል።


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊመንግስትየደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ያለአገልግሎት የተቀመጡ የቢሮ እቃዎች፣ ብረታብረቶች ያገለገሉ የጤና ጣቢያ አልጋዎች እንዲሁም ሌሎች እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሽጥ ይፈልጋል።

 በመሆኑም፣ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልታችሁ መሳተፍ ትችላላችሁ

  1. በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛዉም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው መሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  2. ተጫራቾች አገልግሎት የሰጡ የተሰባበሩ የቢሮ እቃዎች ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን የጤና ጣቢያ አልጋዎች እንዲሁም ሌሎች እቃዎች በፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 601 የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመያዝ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
  3. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታውን ባወጣዉ /ቤታችን በመገኘት የተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ 300 /ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የስራ ስአት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃዎች የሞሉትን 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው
  5. ማንኛውም ተጫራች እቃውን ዋጋ የሞላበትን ብቻ ዋናውን ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ 6 ፎቅ አዳራሽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ደሴ ካራጉቱ ግብርና ግቢ ውስጥ በሚገኘው አስተዳደር አዲሱ ህንጻ ላይ 6 ፎቅ አዳራሽ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 15 ቀናት በኋላ 16ኛዉ ቀን 400 ስአት ታሸጎ በዚሁ ቀን 430 ሰአት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎችን በተዘጋጀዉ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ከዋጋ ግምት በታች መሙላት አይቻልም።
  8. ተጫራቾች በተገለጸው ቦታ ጨረታዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እስከ 1100 ስአት ድረስ እቃዎቹን ባሉበት ቦታ በመሄድ በአካል በማየት ዋጋ መሙላት ይችላሉ።
  9. ርክክቡ የሚፈጸመዉ ደሴ ካራጉቱ ግብርና ግቢ ውሥጥ ነው።
  10. የጨረታዉ አሸናፊ የሆነው በተናጠል በተሰጣቸው የእቃው አይነት መለያ ቁጥር (ኮድ) መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራቾች ይሆናል።
  11. ተጫራቾች በፖስታው ላይ ስም ከነአያት ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለባቸው።
  12. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝብ በአላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  13. ለበለጠ መረጃ የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንበረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 8181 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  14. በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ

ዞን ገንዘብ መምሪያ

Save Tender