Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/
  • Address ጂንካ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline27 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2025-12-27 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ስፖርት ቢሮ የጂንካ ስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከል የስፖርተኞች ቀለብ ምግብ ለመመገብ የሚፈልጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለማሠራት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ስፖርት ቢሮ የጂንካ ስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከል የስፖርተኞች ቀለብ ምግብ ለመመገብ የሚፈልጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግሥት ////ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣የቲን የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፣
  3. የጨረታ አሸናፊ 50% የጨረታ ዋስትና ማስያዝ አለበት፣
  4. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ/ 15/ አሥራ አምስት የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላል፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፣
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህገዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15ኛው ቀን ከቀኑ 900 ሰዓት ታሽጐ በዛኑ ቀን 1000 ሰዓት ይከፈታል፣
  7. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮው ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/

ለበለጠ መረጃ በስልክቁጥር 046-77-52-968 ደውሎ ማረጋገጥ ይችላል።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/

Save Tender