የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሬዲዮ አየር ሰዓት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የሬዲዮ አየር ሰዓት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት የሬዲዮ አየር ሰዓት አገልግሎት ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የግዢ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት Refugees and Returnees Service በሚል የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡበትን ዋጋና የማስረከቢያ ጊዜ ከታች በተገለጸው ሰንጠረዥ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጫራቾች ዋጋ በግልጽ የሚነበብና ድልዝ ስረዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ድልዝ ስርዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሺያል ሰነድ እንድ ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ CPOን ጨምሮ ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀዉ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጥሪ በደረሰው በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት ቀርቦ የሥራ ውል መፈረም አለበት፡፡
- አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአምስት ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
