Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0921770036
  • Website
  • Deadline15 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-01-16 00:00:00
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply , Electronics Materials , Supply Of Animals

በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የዕንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ እና የተለያዩ መኖዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፦ጉ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ፋ/ 04/2018 ዓ.ም

በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ የዕንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ እና የተለያዩ መኖዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የ2 ወር የዕንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ፣

ሎት 3. የዕንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ ማለማመጃ መኖ፣

ሎት 2. የተለያዩ ወተት ላም የተመጣጠነ መኖ፣

ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃ ስካነር ብቻ፣

ስለዚህ በዚህ የሥራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች፡፡

1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣

5. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1. 30,000፣ ሎት 2. 20.000፣ ሎት 3. 20.000፣ ሎት 4. 25.000 የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

6. ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 200 00 / ሁለት መቶ ብር/በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፣

7. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት ቀን በ10ኛ ቀን 11፡30 ይሆናል፡፡

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቦታ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4

9. ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ሕጋዊ ወኪል ለመሆናችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

12. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡ /NAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል፡፡ ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

13. ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣

14. በጨረታው ላይ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል

15. በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል፡፡

16. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው ከተከፈተ በኃላ ናሙና የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

17. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ፡-

ስድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ከ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04

በስልክ ቁጥር፡- 0921770036 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ምርጥ ዝርያ የሆነ የ2 ወር የዕንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ፡፡

የወተት ከብት የተመጣጠነ መኖ እና የዕንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮ ማለማመጃ መኖ ውሉ ለአንድ ዓመት የሚቆይ በተፈለገበት ቀንና ቦታ በራሱ ትራንስፖት ማቅረብ የሚችል፡፡

በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender