ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አክሲዮን ማኅበር ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርክ ሾፕ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ ባሌስትራዎች፣ ሻክል፣ ፕሬዥር ፕሌቶች፣ ካቦዎች፣ የብረት ታንከሮች እና ሌሎች እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር [Gada/NCB/07/2018]
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አክሲዮን ማኅበር ሞጆ በሚገኘው የድርጅቱ ዎርክ ሾፕ ውስጥ የተለያዩ ያገለገሉ ባሌስትራዎች፣ ሻክል፣ ፕሬዥር ፕሌቶች፣ ካቦዎች፣ የብረት ታንከሮች እና ሌሎች እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ኢትዮጵያዊ የሆኑ፣ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ያላቸው እና በማንኛውም ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ሕንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም ወይም በመፈርም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሰጥ 15% ቫት ያካተተ መሆን አለበት ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበትን ዋጋ 2% በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ላይ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነድ የዝዙ ተወዳዳሪዎች የገዙትን ሰነድ እና ደረሰኝ በመያዝ እቃዎችን ሞጀ በሚገኘው የድርጅቱ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል።
- የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት አጠቃላይ ያሸነፉበትን እቃ ሙሉ በሙሉ በመክፈል እቃውን ከግቢ ማውጣት አለባቸው።
- ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ ሞጆ ይገኛሉ፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሑድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ሕንጻ 12ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-558-25-19 ይደውሉ፡፡
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አክሲዮን ማኅበር
