Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/
  • Address ጂንካ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline17 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-01-17 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Hotel Equipment

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ስፖርት ቢሮ የጂንካ ስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከል የስፖርት ሰልጣኝ አትሌቶች ቀለብ ምግብ ለመመገብ የሚፈልጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመመገብ ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ስፖርት ቢሮ የጂንካ ስፖርት ማበልፀጊያ ማዕከል የስፖርት ሰልጣኝ አትሌቶች ቀለብ ምግብ ለመመገብ የሚፈልጉ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመመገብ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1.       የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።

2.       በዘርፉ የተሰማራበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።

3.       የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

4.       የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

5.       በዘርፉ በቂ ልምድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ሆኖ፡-

6.       ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የገንዘብ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ የምገባ የምግብ ዝርዝር ሠነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ማስፈርና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማና ማኀተም በመምታት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7.       ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በማሰብ በተከታታይ 5/ አምስት/ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋይ/ንብ/ አስ/ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።

8.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሊስት /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9.       የጨረታ አሸናፊ 50% የጨረታ ዋስትና ማስያዝ አለበት፣

10.   ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛው ቀን ከቀኑ 900 ሰዓት ታሽጐ በዛኑ ቀን 1000 ሰዓት ይከፈታል፣

11.   ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮው ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፣

12.   መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ /ጂንካ/

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-77-52-968 ደውሉ ማረጋገጥ ይችላል።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባህልና ስፖርት ቢሮ

Save Tender