ገነት ሆቴል የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የዶሮ እና የአሳ ተዋፅኦ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን አወዳድሮ አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የዶሮ፣ የአሳ እና የአትክልትና
ፍራፍሬ የጨረታ ማስታወቂያ
ገነት ሆቴል የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የዶሮ እና የአሳ ተዋፅኦ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን አወዳድሮ አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመ መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
· የ2018 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
· የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፡፡
· የግብር ከፋይ ምዝገባ፣ ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር ሰነድ ያላቸው።
· ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለገነት ሆቴል በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· ተጫራቾች የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ በተናጥል ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እስከ አስረኛ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አስረኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ በቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
· ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ባሉበት በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
· ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 0115-50-47-01 / 0939-500000 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ገነት ሆቴል
