የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት አሸዋ፣ ጠጠር፣ ግንብ ድንጋይ፣ ሀርድ ኮር፣ ሰሌክትድ ማቴሪያል እና ፑሚስ ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የግንባታ ግብዓቶች ከነትራንስፖርቱ የወጣ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 8/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት አሸዋ፣ ጠጠር፣ ግንብ ድንጋይ፣ ሀርድ ኮር፣ ሰሌክትድ ማቴሪያል እና ፑሚስ ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለግንባታ ግብዓቶቹ ከነትራንስፖርቱ ግዥ ለእያንዳንዱ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ጋራንቲና (un conditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ረፋድ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0114621457/0913-56-49-36
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
