በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ አሰላ በሀዋሳ እና ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የምግብ እህል እና የብጣሪ አህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሽ/ 02 ሠነድ/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ አሰላ በሀዋሳ እና ቦንጋ ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-
1. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Supply Sector) ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲሰ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ማንኛው ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፤
5. ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት፡፡ ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
8. የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሠነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።
9. ዋጋውን በኢንቬሎፕ በማሽግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው የካቲት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን የካቲት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ጽ/ቤት አዳራሽ እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
ስልክ ቁጥር 011 6 18 61 25 አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
