በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ አሸዋ እና ድንጋይ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/FW/02/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ አሸዋ እና ድንጋይ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
· ተጫራቾች በኮንስትራክሽን ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
· ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ ቢሮ ወይም ቡሬ ደብረማርቆስ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ወይም በአካውንት ቁጥር 1000252665203 EEP Transmission Substation Construction በማስገባት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
· ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/FW/02/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ቡሬ ደብረማርቆስ የፕሮጀክት አሸዋ፣ ጠጠር እና ድንጋይ የማዕቀፍ ስምምነት ግዥ |
ብር 50,000.00 |
ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ጥር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት |
· ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
· ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251 116 73 21 98 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ
