Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise (የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት) (ኢኢግልድ)
  • Address በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ አራት መንታ በሚወስደው መንገድ ጣልያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት) : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0111281529
  • Websitehttp://www.eiide.com.et/web/guest/about-us
  • Deadline21 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price700.00
  • opening date2026-02-21 00:00:00
  • Categories Cargo Vehicle , Vehicle

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ንብረት የሆነ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ንብረት የሆነ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.     ተጫራች ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባን የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ሃያ በመቶ ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

3.     ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ 16ኛው ቀን 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 410 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና /ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

4.     በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸለት 7 የስራ ቀናት በኋላ 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ በሙሉ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለኢኢግልድ ገቢ ሆኖ ኢኢግልድ ሌላ አማራጭ መጠቀም ይችላል፣

5.     የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 230 እስከ 1030 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ (የቀድሞ ጅንአድ መስሪያ ቤት) አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በመሄድ የተሽከርካሪውን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡

6.     ድርጅቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

አድራሻ፡- አዲስ አበባ በአራዳ ፍለ ከተማ በወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ አራት መንታ በሚወስደው መንገድ ጣልያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ /ቤት)

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ፡- በስልክ ቁጥር 011-3-69-26-84 /011-3-69-19-95 በመደወል ወይም በድረ ገፅ www.mewit.com.et ወይም www.eiide.com.et በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ)

Save Tender